በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ተቋማትን ለመመዘን የ...

image description
- ውስጥ ወቅታዊ ጉዳይ    0

በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ተቋማትን ለመመዘን የሚያስችል የቅድመ ምዘና ክትትል፣ ድጋፍ እና ኢኒስፔክሽን አግባብ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ ኃላፊዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ

መጋቢት 16 ቀን 2017ዓ.ም

በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የማዕከል ተቋማት፣ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች የአፈፃፀም ምዘና ለማከናወን እንዲቻል የቅድመ ምዘና ክትትል፣ ድጋፍ እና ኢኒስፔክሽን አግባብ ላይ ለክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ለክ/ከተማ ፕላንና ልማት ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ለዋና ስራ አስፈፃሚዎች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።

የምዘና ትግበራ ሂደት አተገባበር ሰነድ ያቀረብት የፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ቴድሮስ ታደሰ እንደተናገሩት በጥምረት የሚካሄደው ምዘና በዋናነት በምዘና ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችንና ቅሬታዎችን በመቀነስ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን የምዘና አፈፃፀም ወጥነት እና ተመሳሳይነት ባለው መስፈርት በተቀናጀ መልኩ ለመመዘን እዲቻል ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልፀው የምዘና ትግበራ ሂደት፣ የመዛኝ ኮሚቴ አባላት አደረጃጀት፣ በምዘና ሂደትና ውጤት ላይ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት፣ የድረ ምዘና ስራዎች እና የአስፈፃሚ አካላት ሚና ጨምሮ መሰል ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየት ተሰቶባቸዋል።

ከዚህም ጋር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውትሶርስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም ሶስቱ ተቋማት ባስቀመጡት አቅጣጫ የተለያየ እና ድግግሞሽ ያለው የምዘና ሂደት ያከናውኑ እንደነበር አስታውሰው ተቋማትን ወደ ተቀራረበ አፈፃፀም እንዲመጡ ለማድረግ ወጥነት ያለው የምዘና ስርዓት መዘርጋቱን ገልፀዋል።

የመድረኩን ማጠቃለያ እና የቀጣይ አቅጣጫ የሰጡት የከንቲባ ፅ/ቤት የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይነህ አመርጎ የምዘና ሂደቱ የተቀመጠውን መስፈርት ተከትሎ የሚከናወን በመሆኑ ስራዎችን በብቃት የሚፈፅሙትን ተቋማት ለማበረታታት እና ክፍተት የሚታይባቸውን ተቋማት የማሻሻያ እርማት እንዲወስዱ ለማድረግ እንዲቻል መሆኑን ገልፀው በእውቀት ላይ የተመሰረተ ለአንድ አላማ የሚከናወን ምዘና በመሆኑ ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በትኩረት እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.