ቢሮው አዲስ የሎጎ መለያ ይፋ አደረገ፡፡

image description
- ውስጥ ወቅታዊ ጉዳይ    0

ቢሮው አዲስ የሎጎ መለያ ይፋ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከፌደራል መንግስት ጠሪ መስሪያ ቤቶች ጋር የተናበበ አዲስ ተቋማዊ የሎጎ መለያ ይፋ አድርጓል፡፡

የቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደተናገሩት አዲሱ ሎጎ ከተቋሙ ሪፎርም ጋር ተጣጥሞ፤ በከተማ አስተዳደሩ አዋጅ ቁጥር 84/2016 ዓ.ም ከተሰጠው ስልጣን እና ኃላፊነት ጋር ተናቦ እንዲሁም ከጠሪ የከተማ አስተዳደሩ እና የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር የተናበበ መሆን ታምኖበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

አቶ አደም ኑሪ አያይዘውም ሎጎዉ የተዘጋጀው ለተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጡ የገፀ-ምድራዊ ፕላን አዘገጃጀት፣ የፕላን አፈፃፀም ክትትል ስራዎች፣ የከተማውን ማህበራዊ ምጣኔ ሀብታዊ የልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ አፈፃፀም እና ክትትል ስራዎችን ሊያሳይ በሚችል መልኩ ነው ብለዋል፡፡ 

በቢሮው የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ተረፈ በበኩላቸው አዲሱ የተቋሙ ሎጎ የፕላንና ልማት እሳቤዎችን እንዲሁም የከተማዋን መዋቅራዊ ፕላን የከተማ ፕላን ህግ ምጣኔ ድንጋጌዎች ባከተተና ታሳቢ ባደረገ መንገድ ነው ብለዋል፡፡  ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ በተቋም አመራሮች፣ ሠራተኞችና በተለያዩ አካላት አስተያየት ተሰጥቶበትና በእርማት ዳብሮ ይፋ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ 

በቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ንጉሴ ሎጎዉ የተቋሙ ገፀ-ምድራዊ(spatial)፣ ማህበረምጣኔ-ሀብታዊ ተግባራት አካላዊ መልክ ሲሆን ተቋሙን ከሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች/ተቋማት/ አንፃር የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሳወቅ እና ለመንገር የምንጠቀምበት ተቋማዊ ልዩ ምልክት፣መልክና  አርማ ነው ብለዋል፡፡
ሎጎዉ ተቋማዊ ሪፎርሙን በሚመጥን መልኩና የተቋሙን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ በከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ ተቋማት ለተቋሙ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራትን ባቀፈ መልኩ መዘጋጀቱንም አክለዋል፡፡ 

በቢሮው የከተማ መሰረተ ልማት ቅንጅት ፕላን ዝግጅትና አጽዳቂ ቡድን መሪ አቶ በረከት ፍቃዱ በበኩላቸው አዲሱ የተቋሙ ሎጎ የተዘጋጀው የመዋቅራዊ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ድንጋጌዎች (30% ለመንገድ መርበብ፣ 30% ለአረንጓዴ ልማትና ተያያዥ መሰረተልማቶች እና 40% ለግንባታ ክፍል የተደነገገን የከተማ ፕላን ምጣኔ ህግን) ተከትሎና  ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ሎጎዉ ላይ የተቀመጡ የግራፊክስ ንድፎች(graphical patterns), የቀለሞች ምርጫ፣ ምልክቶች ትርጉምም ከከተማዋ የመሬት አጠቃቀም  አንፃር ቁልፍ ፍቻቸው እንደተቀመጠና በቀጣይም ተቋሙ የሎጎዉ ብቸኛ የአዕምሮ ንብረት ባለቤት መሆኑን ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ከቢሮዉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ 

                      “በፕላን የምትመራ፤ ዘመናዊ ከተማ” 
 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.